የተፋሰስ ከፍተኛ ምክር ቤት 5ተኛ መደበኛ ጉባኤ ተካሔደ

 በስብሰባውም ሶስቱ የተፋሰስ ባለስልጣን (አዋሽ፣አባይ እና ስምጥ ሸለቆ ሀይቆች)በ2009 በጀት አመት የተከናወኑ ተግባራት እና  በ2010 በጀት ዓመት ሊሰሩ ያቀዱዋቸውን የእቅድ ክንውኖች ለተሰብሳቢዎች በማቅረብ  በቀጣይ  ለሚሰሩት ስራ ግብዓት የሚሆን ሀሳብ ከተሳታፊዎች ወስደዋል፡፡ እንዲሁም መ/ቤታችን የዝዋይ ሻላ ን/ተፋሰስ የመጀመሪያ ደረጃ  የተፋሰስ እቅድ እና የአጠቃላይ የተፋሰስ የእቅድ ማእቀፍ አቅርቧል፡፡ በቀረቡት ሰነዶች ላይም  ውይይት  የተደረገ ሲሆን የተፋሰስን ስራ በመቀናጀት መሰራት አስፈላጊ እንደሆነ ሁሉም ተሳታፊዎች አጽንኦት የተሰጠት ጉዳይ ሆኖዋል፡፡  በመጨረሻም  የኢፌድሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የተፋሰስ ከፍተኛ ም/ቤት ሰብሳቢ ክቡር አቶ  ደመቀ መኮንን የወደፊት አቅጣጫ በማስቀመጥ የእለቱ ስብሰባ ተጠናቋል፡፡