የዉስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት

የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት

2.1 ቅድሚያ የምንሰጣቸውን ተግባራት ከመስሪያ ቤቱ ዓላማ ጋር የተጣጣሙ  መሆናቸውን በማረጋገጥ ሥጋት ተጋላጭነት ያለባቸውን የመስሪያ ቤቱን የስራ ክፍሎች  መሰረት ያደረገ ዕቅድ ከሰው ኃይል አመዳደብ እና ከወጪ በጀት ፍላጎት ጋር አጠቃሎ በማዘጋጀት ለመስሪያ ቤቱ  የበላይ ኃላፊ አቅርቦ ማፀደቅና የኦዲት የስራ ትዕዛዝ  እና ሃሳብ በመስጠት እቅድና ኘሮግራም የማዘጋጀት፡፡

2.2 የፀደቀውን እቅድ በዚህ መመሪያ አንቀጽ 10 ንዑስ አንቀጽ 2 በተመለከተው መሰረት አዘጋጅቶ ለሚኒስትሩ የማቅረብ ፡፡

2.3 የውስጥ ኦዲቱን መደበኛ የኦዲት ዕቅድ ሁሉም የኦዲት ተደራጊው የስራ ክፍሎች እንዲያውቁት የማድረግ

2.4 ኦዲተሮች ተለይቶ የሚሰጣቸውን የኦዲት ስራ በብቃት ለማከናውን የሚያስችላቸው ዕውቀት ልምድ ክህሎትና ሌሎች ተፈላጊ ችሎታዎች እንዲኖራቸው የማድረግና የስልጠና ፍላጎቶችን በማፀደቅ በበላይ ኃላፊ አፈፃፀሙን የመከታተል ፡፡

2.5 የተዘረጋው  የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት የመስሪ ቤቱን ዓላማዎች በከፍተኛ ቁጠባና ውጤታማ በሆነ መንገድ ከግብ ለማድረስ ማስቻሉን በቂ መረጃዎችን ሰብስቦ በመገምገምና በቁጥጥር ስርዓቱ ላይ ያለውን ስጋት ወይም ተጋላጭነትን በመለየት ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ የማሳወቅ፡፡

2.6  በፀደቀው እቅድ መሰረት የኦዲት መጀመሪያ ስብሰባ እና ኦዲቱን አከናውም የኦዲት ማጠናቀቂያ ስብሰባ ከሚመለከታቸው ሰራተኞችና የስራ ኃላፎዎችና የመስሪያ ቤቱ በላይ ኃላፊ ጋር የማድረግ ፡፡

2.7  የተደረሰበትን ውጤት ደምዳሜና የማሻሻያ ሃሳብ በሪፓርት ተገቢ ባህሪያት መሰረት የተሟላ ሪፓርት አዘጋጅቶ ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ የማቅረብ፡፡

2.8. አስቀድሞ በዕቅዱ ያልተያዘ ልዩ ኦዲት እንዲያደርግ በመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ሲታዘዝ ኦዲት የማከናወን፡፡

2.9  በበጀት ዓመቱ መጨረሻ በመስሪያ ቤቱ አማካይነት የተደረገው ቆጠራ በፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ ደንብና መመሪያዎች መሰረት መከናወኑን በማረጋገጥ የቆጠራ ሪፓርቱን ከቆጠራ ሰነድ ጋር ለሚኒስቴር እንዲቀርብ ማድረግ ይህንንም ለማረጋገጥ በቆጠራ ወቅት በታዛቢነት የመገኘት በፈሰስ ሂሳብ ስራ ላይ የመሳተፍ፡፡

2.10  ቀድሞ በቀረቡት የኦዲት ሪፓርት መሰረት የእርምት እርምጃ ያልተወሰደባቸው ግኝቶች በመከታተል የእርምት እርምጃ እንዲወሰድባቸው ለመስሪያ ቤቱ በላይ ኃላፊ የማሳሰብ፡

2.11. የውጪ አዲተሮች በሚያቀርባቸው ግንቶች ላይ የእርማት እርማጃዎች እንዲወሰድ ክትትል የማድረግ

2.12.  በውስጥ አዲት የተከናወኑ ተግባራትን የሚገልጽ ወቅታዊና አመታዊ የስራ አፈጻፀም ሪፓርት ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ የማቅረብ ኃላፍነት አለበት፡፡