ከፍተኛ ምክር ቤት ሴክሬታሪያት የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

የስምጥ  ሸለቆ ሐይቆች  ተፋሰስ  የደቡብ  ብሔር  ብሔረሰቦች  እና  የኦሮሚያ  ክልሎችን የሚያጋራ ሲሆን  በምዕራብ  የኦሞ-ጊቤ  ወንዝ  ተፋሰስ፣በደቡብ  የኬንያ  ሪፐብሊክን፣ በምስራቅ ዋቢ ሸበሌ  እና  ገናሌ  ዳዋ ተፋሰሶች  እንዲሁም  በስተስሜን  የአዋሽ  ተፋሰስ  አዋሳኙ ናቸው፡፡በዚህ ተፋሰስ  ውስጥ ዝዋይ፣ ላንጋኖ አብያታ፣ ሻላ፣አዋሳ፣ አብያ፣ ጫሞ እና ጨው ባህር ሃይቆች  ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ12 ተፋሰሶች  የተቀናጀ  የተፋሰስ ልማት ከሚካሄድባቸው  አካባቢዎች  የስምጥ  ሸለቆ ሐይቆች  አንዱ ነው፡፡ የተቀናጀ የተፋሰስ ሰራዎች በስፋት በመከናወኑ በተፋሰሱ ላይ የተጋረጠውን የድርቅና የአካባቢ መራቆት ስጋት ለመቀነስ ባለስልጣን መ/ቤቱ በየዘርፉ ጉልህ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በመሆኑም   በመ/ቤቱ የተከናወኑ ውጤታማ አፈፃፀሞችን እና ተፋሰሱ ላይ የሚታዩትን ችግሮች  በኮሚኒኬሽን ስራዎች እንዲታጀቡ በማድረግ በአንድም ይሁን  በሌላ  በኩል  ለቀጣይ ስራዎች መቃናት በጎ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡

የኮሚኒኬሽንም ስራ ለአንድ ተቋም የገጽታ ግንባታናተቋሙ ዕለት ተዕለት የሚያከናውናቸውን ተግባራት ለህብረተሰቡ፣ለመንግስትና ለባለድርሻ አካላት ለማስተዋወቅ ዋነኛ መሳሪያ ሲሆን ጥሩ የሆነ የስራ ግንኙነት እንዲፈጠርም ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው እሙን ነው፡፡ በመሆኑም የስምጥ ሸለቆ ሐይቆች ተፋሰስ ባለስልጣን የከ/ም/ቤት/ሴ/የህ/ግ/ ዳይሬክቶሬት በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ሲሆን፤ከሚያከናውናቸው ተግባራት ውስጥ፤-የባለስልጣን መ/ቤቱን ዓላማና ተልዕኮ ለማሳካት በተፋሰሱ ውስጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለህብረተሰቡ  ማሳወቅ፤የተለያዩ ሚድያዎችን እና የህትመት ውጤቶችን በመጠቀም የገፅታ ግንባታ መፍጠር፤በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ፕሬስ ሪሊዝ፣ፕሬስ ኮንፍረንስና ብሪፊንግ በማዘጋጀት ማቅረብ፤ በህዝብ ዘንድ እንዲታወቁ የሚፈለጉ መረጃዎች ተደራሽ የሚሆኑበትን የስርጭት አውታሮችን በማጥናት ያቀርባል፣የተቋሙን ገጽታና ጥቅም የሚጎዱ ዘገባዎች በመገናኛ ብዙሃን ሲወጡ ከሚዲያ ሞኒተሪንግ ውጤቶች ላይ በመነሳት ተቋሙ በትክክለኛ ገጽታው እንዲታወቅ ምላሽ ያዘጋጃል፣የመ/ቤቱን ሥራ በህዝብ ዘንድ እንዲታወቁናተደራሽ የሚሆኑበትን የስርጭት አውታሮችን ማጥናት፣ወቅታዊ የመስሪያ ቤቱን መረጃዎች አደራጅቶ ማስቀመጥና ለህዝብ ጆሮ እንዲደርስ ማድረግ፤በ/መቤቱ የሚከናወኑ/ የሚደረጉ የስብሰባና የውይይት መድረኮችን የሚድያ ሽፋን እንዲያገኙ ማድረግና ለህዝብ ጆሮ ማድረስ፤በመንግስት ከፍተኛ አካላት የተሰጡ መግለጫዎችን አስመልክቶ ከህዝብ አስተያየትና ከሚዲያ ሞኒተሪንግ ተሰብስበውና ተደራጅተዉ የተተነተኑ መረጃዎች ሲቀርቡለት ምላሽ እንዲሰጥበት ከሙያዊ አስተያየት ጋር በማዘጋጀት ለበላይ ሀላፊ ያቀርባል፣መረጃ ለሚጠይቁ አካላት ትክክለኛና እውነተኛ መረጃ በማጠናቀር ለጠያቂዎች ያቀርባል፤መስሪያ ቤ/ቱ የሚሰራቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን በተመለከተ ጥናት ማካሄድ፤ ለህዝብ የመረጃ ምንጭ የሚሆኑ መረጃዎችን በተደራጀ መልኩ እንዲያዙና ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ ህዝቡ በንቃት እንዲሳተፍና እንዲደግፍ ማድረግ ዋነኛ ተግባራት ናቸው፡፡