የተፋሰስ ዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት

የተፋሰስ እቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዋና ተግባር በስምጥ ሸለቆ ሐይቆች ተፋሰስ ውስጥ የተቀናጀ የውሃ ሃብት አስተዳደር ለማስፈን የሚረዱ ጥናቶችንና ፕሮጄክቶችን ተግባራዊ ማደረግና የባለስልጣን መ/ቤቱ ዓመታዊ የእቅድ ትግበራ ላይ ወጥነት ያለው የክትትልና ግምገማ ስርዓትን መዘርጋት ነው፡፡ ዳይሬክቶሬቱ የታቀዱ ተግባራት በታቀደው መጠን፣ የጊዜ ሰሌዳ እና በጀት መሠረት መፈጸማቸውን ማረጋገጥ፣ የዓቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፣ የተቋሙን ስትራተጂክና ዓመታዊ ዕቅድ ማዘጋጀት፣ የሚዘጋጀውን የተፋሰስ እቅድ ማስተባበር፣ የፕሮጀክት እቅድ ማዘጋጀት፣ የዕቅድ አፈጻጸሞችን መከታተል መገምገም እና ግብረ መልስ መስጠት፣ ዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ እና ምርምር ተቋማትን ተስስር ማጠናከር፣ የተፋሰስ ጥናትና ምርምር ከፍተቶችን መለየት የጥናት ፕሮፖዛል ማዘጋጀት፣ የተለያዩ የተፋሰስ የጥናትና ምርምር ሰነዶችን ማሰባሰብና ማደራጀት ከዋና ዋና ስራዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

በዚህ መሰረት ባለስልጣን መ/ቤቱ በሁሉም የስራ ዘርፍ የዕቅድ አፈጻጸም መለኪያዎችን በማዘጋጀት በየደረጃው ያለ ፈጻሚ አካል የተሰጠውን ተግባር በአግባቡ እየፈጸመ መሆኑን መከታተልና መቆጣጠር  ሲሆን ፈጻሚዎች በየደረጃው ወቅታዊ የሥራ ግምገማ ማከናወናቸውን በመከታተል የተካሄደው የሥራ ግምገማ ምን ያህል ችግር ፈቺና አቅጣጫ ጠቋሚ እንደሆነ በመመዘንና ድጋፍ በማድረግ የክትትልና ግምገማ ስርዓትን በተፋሰስ ዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት በኩል  ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል ፡፡

ከሚቀርበው ሪፖርት በተጨማሪ በመስክ በመገኘት ድጋፍ መስጠትና ዕቅዶች በተቀመጠላቸው መስፈርትና ጊዜ መሠረት መፈጸማቸውን ይገመግማል፤ በየወሩና በየሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም መከታተያ ቼክ ሊስት አዘጋጅቶ በቼክ ሊስቱ መሠረት በየጊዜው በተመረጡ ተፋሰሶች በመገኘት ክትትልና ግምገማ እያደረገ ይገኛል፡፡

በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም፣ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ረቂቅ ዕቅድ ላይ ከአጠቃላይ የመ/ቤቱ ሰራተኞች ጋር ውይይት በማካሄድ ጠቃሚ ግብዓቶች ተሰብስበው የአምስት ዓመት (2008 – 2012) የመ/ቤቱ ስትራቴጅክ ዕቅድ ተዘጋጅቷል፡፡  የተፋሰስ ዕቅድ ለማዘጋጀት የሚረዳ ፍኖተ ካርታ በተፋሰስ ዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳ/ት  አስተባባሪነት በማዘጋጀትና የባለሞያዎች ቡድን በማቋቋም ረቂቅ የተፋሰስ ዕቅድ ሰነድ ለዝዋይ-ሻላ ንዑስ ተፋሰስ እንዲሁም የተጠቃለለ የተፋሰስ እቅድ ማዕቀፍ ለአጠቃላይ ተፋሰሱ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡

የተለያዩ የዓቅም ግንባታ ሥልጠናዎች በተለይ በካፒታል ፕሮጀክት አዘገጃጀት እና በፕሮግራም በጀት አዘገጃጀት ላይ በስራ ክፍሉ አስተባበሪነት ለመ/ቤቱ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በዚህ መሰረት የካፒታል ፕሮጀክት ዕቅዶች በሚከተሉት ርዕሶች ተዘጋጅተዋል፡- Cheleleka wetland Conservation and Rehabilitation project through Community based Management Approach;  Minimizing environmental pollution released from the main sources (domestic solid waste, domestic wastewater, industrial wastewater, and non-point pollution from farm land) in the rift valley lakes basin using waste management best practices. ሌላው ሳይንሳዊና ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ቅንጅታዊ የአሰራር ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ የትምህርትና ሥልጠና፣ የምርምር ተቋማትና ኢንዱስትሪ ትስስር ፎረም ዩኒቨርስቲዎችንና የምርምር ተቋማትን ማዕክል በማድረግ ተመስርቷል፡፡