የዩኒቨርሲቲ – እንዱስትሪ የትስስር ፎረም አባላት ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡

በተፋሰሱ ዉስጥ ከሚገኙ ከተለያዩ የትምህርትና ስልጠና፣ የምርምር ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች ጋር ትስስር በመፍጠር፣ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ችግር ፈቺና ሁሉን አቀፍ ፕሮጀክቶችንና ፕሮግራሞችን ለማዘጋጀት እንዲሁም የምክክርና ድጋፍ ሥራዎችን ለማከናወን ያስችለው ዘንድ በስምጥ ሸለቀ ሀይቆች ተፋስስ ባለሥልጣን አዘጋጅነት    ዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር ፎረም ስብሰባ በተለያየ ጊዜያት  የተካሄደ ሲሆን  ስብሰባውና የምክክር መድረኩ ቀጣይነትና ዘላቂነት ያለው በመሆኑ ባለስልጣን መ/ቤቱ በተፋሰሱ ውስጥ  ያሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትንና የምርምር ማዕከላትን (ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ፣አርሲ ዩኒቨርስቲ፣ወለቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና አባምንጭ ዩኒቨርስቲ) የተሳተፉ ሲሆን ምሁራኑ     ተፋሰሱ ላይ የሚታዩ ችግሮችን የሚያሳይ በርካታ ጽሁፎችን አቅርበዋል

በቀረበው ጽሁፍ ላይም ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገ ሲሆን ቀድሞ በነበረው ትስስር ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮች ላይም በመነጋገርና በመተማመን በቀጣይ በዘላቂነት በተጠናከረ መንገድ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ይህንንም ለማድረግ ያስችል ዘንድ ከቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፎች መነሻነት  ዩኒቨርስቲዎቹ ባላቸው እውቀትና አቅም ድጋፍ በማድረግ በተፋሰሱ የሚታዩ አንኳር ችግሮችን ለመቅረፍ ሁሉም የድርሻቸውን ለመወጣት የስራ ድርሻ  በመከፋፈል  ለቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

በእለቱም የተፋሰስ ባለስልጣን መ/ቤቱ የ2010 በጀት ዓመት የዩኒቨርሲቲ- ኢንዱስትሪ ትስስር ዕቅድ አፈፃፀም በ9 ወራት የተሰሩ ስራዎችና በአፈፃፀም ወቅት ያጋጠመውን ችግርና የተወሰደውን መፍትሄ በማከል ለታዳሚያን በባለስልጣ መ/ቤቱ የተፋሰስ እቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ተከተል ታደሰ ቀርቧል፡፡  

በመጨረሻም በተሳታፊዎች በተነሱ ማለትም በቀጣይ መሰራት ባለባቸው የስራዎች ድግግሞሽ እንዳይኖር ፣ቅንጅታዊ ስራዎች እንዲጠናከሩ፣ልምድ ልውውጦች እንዲካሄዱ፣ለጥናት ምርምር የበጀት ምንጭ ሚገኝበት ሁኔታ በባለስልጣን መ/ቤቱ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሰራበት አስተያየት የተሰጠ ሲሆን አያይዘውም ስለወደፊት የግንኙነት ድግግሞሽና ውጤታማ ቅንጅት በመፍጠር መስራት እንዲቻል በመስማማት የዕለቱ ውይይት መድረክ ተጠናቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *