የአባያ ጫሞ ሀይቆች በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች መዳረጋቸው ተገለጸ

ከ180 ሄክታር በላይ በሆነ የሀይቆቹ ዳርቻ መሬት ላይም የእምቦጭ አረም መከሰቱ ታውቋል

የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ተፋሰስ ባለሥልጣን በአባያ ጫሞ #ሰገንና ወይጦ ንዑስ ተፋሰስ በውጤታማ የውሃ ሀብት አያያዝና አጠቃቀም ዙሪያ ከተለያዩ ባለድርሻ  አካላት ጋር የመከረ ሲሆን\ በመድረኩም ላይ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኢነተር ዩኒቨርስቲ ኮርፖሬት ፕሮግራም ማናጄር ዶ/ር ፋሲል እሸቱ በተፋሰሱ ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት መጠን መንስኤና መፍትሄ አስመልክተው ጥናት አቅርበዋል።

የእንቦጭ አረምን ጨምሮ በተለያዩ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች የውሃ መጠናቸውንና ጥራታቸው ለአደጋ ከተደረጉት የተፋሰሱ አከባቢዎች መካከል ደግሞ በቱሪስት መስህብነታቸው የሚታወቁት የአባያና የጫሞ ሀይቆች መሆናቸወን ጥናቶቹ አሳይተዋል።

በላይኛው ተፋሰስ አከባቢዎች የተጠናከረ የአፈርና የውሃ ጥበቃ  ስራ ባለመሰራታቸው የተነሳ  በጎርፍ ደለል መሞላታቸው  የሀይቆቹ \ዳርቻዎች በእርሻ ስራ #ግጦሽ #ደን ጭፍጨፋና በመሳሰሉት ተግባራት ከሰውና እንስሳት ንክኪ ነፃ ያለመሆናቸው  ለሃይቆቹ መጠን መቀነስ ምክንያቶች ከሆኑት መካከል ዋነኞቹ እንደሆኑም በጥናቶቹ ተመልክቷል።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ ከ800 ሜትር በላይ ርዝመት ያለው የሀይቆቹ አካል ውሃው ነጥፎ ወደ ደረቅ መሬትነት እንደተለወጠ ጥናቱ ያሳያቸው የአባያና ጫሞ ሀይቆች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከ187 ሄክታር በላይ የቆዳ ስፋት ያለው የእንቦጭ አረም በሀይቆቹ ዳርቻዎች በፍጥነት እየተዛመተ መገኘቱ ለሀይቆቹ መድረቅ ሌላውና ትልቁ ስጋት ሊሆን እንደሚችልም በጋሞ ጎፋ ዞን አከባቢና ደን ጥበቃ ጽ/ቤት  የብዝሃ ህይወት ልማት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ ጋመቡራ ገንታ ባቀረቡት ጽሁፍ አሳይተዋል።

የአከባቢውን ህዝብ በዋነኛነት በማሳተፍ አረሙን ለማስወገድና ለመከላከል ስራዎች የተጀመሩ ቢሆንም አዞና ጉማሬን ጨምሮ ሃይቆቹ ከሏቸው አደገኛ እንስሳት አንፃር በሰው ጉልበት ብቻ የማይደፈር በመሆኑ መንግስትና ባለድርሻ አካላት አፋጠኝ ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባም መድረኩ ትኩረት ሰጥቶታል።

የስምጥ ሸለቆ ሃይቆች ተፋሰስ ባለስልጣን በተፋሰሶቹ አከባቢ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል መጠነ ሰፊ ሥራዎች ሲያከናውን የቆየ ቢሆንም በሚፈለገው ፍጥነት አደጋዎቹ ሲቀነሱ ባለመቻላቸው ትልቅ ስጋት ውስጥ መሆናቸው የገለፁት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ከበደ ካንቹላ ባለድርሻ አካላት ህዝቡን አቀናጅቶ በማነቃነቁ ረገድ ትኩረት ሰጥተው ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የተከሰተውን አሳሳቢ ችግር በዘላቂነት ለማስወገድ ባለስልጣኑ በቴክኒክ እና በፋይናንስ ለባለድርሻ አካላት ሲያደርግ የቆየውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ በሀይቆች ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው ጉዳት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አመራሩና ህዝቡ ተገንዝቦ ተፋሰሶችን ከአደጋዎች ሊታደግ ይገባል ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *