የሀይድሮሎጂ መረጃ መሰብሰቢያ ጣቢያዎች ላይ ለሚሰሩ አንባቢዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡

በስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ተፋሰስ ባለሥልጣን ስር ላሉ የሐይድሮሎጂ ጣቢያዎች መረጃ ለሚሰበስቡ አንባቢዎች  የሀይድሮሎጂ መረጃዎችን አሰባሰብና ጥቅሞችን በተመለከተ በሀዋሳ ፒና ሆቴል ስልጠና ተሰጠ፡፡

በዕለቱም የባለሥልጣን መ/ቤቱ የተፋሰስ ጥናት፣ምርምር እና መረጃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቸርነት መሀሪ በመክፈቻ ንግግር የተከፈቱ ሲሆን በንግግራቸውም ውሃ ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት መፋጠን የሚያበረክተው አስተዋጽኦ  ከፍተኛ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን ፡፡

ስለዚህ ይህንን ውስን ሀብታችንን ተገቢ የሆነ የአጠቃቀም ስርዓት  እንዲኖር የተጠናከረ መረጃ አያያዝ ስርዓት ካልተዘረጋ የውሃ ሀብታቶቻችን በተለይ በሐይቀቆቻችን ፣በግድቦቻችን እና በወንዞቻችን ላይ በመጠንም ይሁን በጥራታቸው ላይ  ከፍተኛ ችግር ውስጥ መውደቃቸው  እንደማያጠራጥር ጠቅሰዋል፡፡ እንዲሁም ወንዞቻችንም  ሆኑ ሀይቆችችን በከፍተኛ የዝናብ ወቅት በጎርፍ አማካኝት በንብረት እንዲሁም በህይወት የሚያደርሱት ጉዳት ለማስቀረት ጥራት ያለው መረጃ በጣም አስፈላጊ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዕለቱም በባለስልጣን መ/ቤቱ ባለሙያዎች በአቶ በየነ ምንዳ  እና በአቶ ብርሀኑ ለገሰ የሀይድሮሎጂ መረጃዎችን አሰባሰበና ጥቅሞቻቸው ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ የቀረበ ሲሆን  በቀረበውም ሰነድ ላይም ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተዋል፡፡ ለተነሱትም ጥያቄዎችና አስተያየቶችም  ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

በመጨረሻም የውሃ ሀብቶቻችንን ለላቀ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማዋል የተጋረጠባቸውን ችግር በጥልቀት በመረዳት የመፍትሄ እርምጃ ለመውሰድ ይረዳ ዘንድ በአንባቢያን በኩል ሚሰበሰብ መረጃ ትልቅ ሚና ስላለው የሚሰበስቡት መረጃ እውነተኛና መሰብሰብ ባለበት ጊዜና ሰዓት መረጃውን በመሰብሰብ የበኩላቸውን  አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እና ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት በአግባቡ በመጠቀም ያለባቸውን ኃላፊነት በታማኝነትና በትጋት  እንዲወጡ የባለስልጣን መ/ቤቱ የጥናት፣ምርምር እና መረጃ አስተዳደር ዳ/ዳይሬክተር አቶ ቸርነት መሀሪ   በማሳሰብ  የዕለቱ ስልጠና አጠቃለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *