የሀይድሮሎጂ መረጃ መሰብሰቢያ ጣቢያዎች ላይ ለሚሰሩ አንባቢዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡

በስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ተፋሰስ ባለሥልጣን ስር ላሉ የሐይድሮሎጂ ጣቢያዎች መረጃ ለሚሰበስቡ አንባቢዎች  የሀይድሮሎጂ መረጃዎችን አሰባሰብና ጥቅሞችን በተመለከተ በሀዋሳ ፒና ሆቴል ስልጠና ተሰጠ፡፡

በዕለቱም የባለሥልጣን መ/ቤቱ የተፋሰስ ጥናት፣ምርምር እና መረጃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቸርነት መሀሪ በመክፈቻ ንግግር የተከፈቱ ሲሆን በንግግራቸውም ውሃ ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት መፋጠን የሚያበረክተው አስተዋጽኦ  ከፍተኛ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን ፡፡

ስለዚህ ይህንን ውስን ሀብታችንን ተገቢ የሆነ የአጠቃቀም ስርዓት  እንዲኖር የተጠናከረ መረጃ አያያዝ ስርዓት ካልተዘረጋ የውሃ ሀብታቶቻችን በተለይ በሐይቀቆቻችን ፣በግድቦቻችን እና በወንዞቻችን ላይ በመጠንም ይሁን በጥራታቸው ላይ  ከፍተኛ ችግር ውስጥ መውደቃቸው  እንደማያጠራጥር ጠቅሰዋል፡፡ እንዲሁም ወንዞቻችንም  ሆኑ ሀይቆችችን በከፍተኛ የዝናብ ወቅት በጎርፍ አማካኝት በንብረት እንዲሁም በህይወት የሚያደርሱት ጉዳት ለማስቀረት ጥራት ያለው መረጃ በጣም አስፈላጊ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዕለቱም በባለስልጣን መ/ቤቱ ባለሙያዎች በአቶ በየነ ምንዳ  እና በአቶ ብርሀኑ ለገሰ የሀይድሮሎጂ መረጃዎችን አሰባሰበና ጥቅሞቻቸው ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ የቀረበ ሲሆን  በቀረበውም ሰነድ ላይም ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተዋል፡፡ ለተነሱትም ጥያቄዎችና አስተያየቶችም  ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

በመጨረሻም የውሃ ሀብቶቻችንን ለላቀ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማዋል የተጋረጠባቸውን ችግር በጥልቀት በመረዳት የመፍትሄ እርምጃ ለመውሰድ ይረዳ ዘንድ በአንባቢያን በኩል ሚሰበሰብ መረጃ ትልቅ ሚና ስላለው የሚሰበስቡት መረጃ እውነተኛና መሰብሰብ ባለበት ጊዜና ሰዓት መረጃውን በመሰብሰብ የበኩላቸውን  አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እና ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት በአግባቡ በመጠቀም ያለባቸውን ኃላፊነት በታማኝነትና በትጋት  እንዲወጡ የባለስልጣን መ/ቤቱ የጥናት፣ምርምር እና መረጃ አስተዳደር ዳ/ዳይሬክተር አቶ ቸርነት መሀሪ   በማሳሰብ  የዕለቱ ስልጠና አጠቃለዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ – እንዱስትሪ የትስስር ፎረም አባላት ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡

በተፋሰሱ ዉስጥ ከሚገኙ ከተለያዩ የትምህርትና ስልጠና፣ የምርምር ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች ጋር ትስስር በመፍጠር፣ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ችግር ፈቺና ሁሉን አቀፍ ፕሮጀክቶችንና ፕሮግራሞችን ለማዘጋጀት እንዲሁም የምክክርና ድጋፍ ሥራዎችን ለማከናወን ያስችለው ዘንድ በስምጥ ሸለቀ ሀይቆች ተፋስስ ባለሥልጣን አዘጋጅነት    ዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር ፎረም ስብሰባ በተለያየ ጊዜያት  የተካሄደ ሲሆን  ስብሰባውና የምክክር መድረኩ ቀጣይነትና ዘላቂነት ያለው በመሆኑ ባለስልጣን መ/ቤቱ በተፋሰሱ ውስጥ  ያሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትንና የምርምር ማዕከላትን (ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ፣አርሲ ዩኒቨርስቲ፣ወለቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና አባምንጭ ዩኒቨርስቲ) የተሳተፉ ሲሆን ምሁራኑ     ተፋሰሱ ላይ የሚታዩ ችግሮችን የሚያሳይ በርካታ ጽሁፎችን አቅርበዋል

በቀረበው ጽሁፍ ላይም ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገ ሲሆን ቀድሞ በነበረው ትስስር ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮች ላይም በመነጋገርና በመተማመን በቀጣይ በዘላቂነት በተጠናከረ መንገድ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ይህንንም ለማድረግ ያስችል ዘንድ ከቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፎች መነሻነት  ዩኒቨርስቲዎቹ ባላቸው እውቀትና አቅም ድጋፍ በማድረግ በተፋሰሱ የሚታዩ አንኳር ችግሮችን ለመቅረፍ ሁሉም የድርሻቸውን ለመወጣት የስራ ድርሻ  በመከፋፈል  ለቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

በእለቱም የተፋሰስ ባለስልጣን መ/ቤቱ የ2010 በጀት ዓመት የዩኒቨርሲቲ- ኢንዱስትሪ ትስስር ዕቅድ አፈፃፀም በ9 ወራት የተሰሩ ስራዎችና በአፈፃፀም ወቅት ያጋጠመውን ችግርና የተወሰደውን መፍትሄ በማከል ለታዳሚያን በባለስልጣ መ/ቤቱ የተፋሰስ እቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ተከተል ታደሰ ቀርቧል፡፡  

በመጨረሻም በተሳታፊዎች በተነሱ ማለትም በቀጣይ መሰራት ባለባቸው የስራዎች ድግግሞሽ እንዳይኖር ፣ቅንጅታዊ ስራዎች እንዲጠናከሩ፣ልምድ ልውውጦች እንዲካሄዱ፣ለጥናት ምርምር የበጀት ምንጭ ሚገኝበት ሁኔታ በባለስልጣን መ/ቤቱ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሰራበት አስተያየት የተሰጠ ሲሆን አያይዘውም ስለወደፊት የግንኙነት ድግግሞሽና ውጤታማ ቅንጅት በመፍጠር መስራት እንዲቻል በመስማማት የዕለቱ ውይይት መድረክ ተጠናቋል፡፡

INVITATION FOR EXPRESSION OF INTEREST

INVITATION FOR EXPRESSION OF INTEREST
FDRE Rift Valley Lakes Basin Authority (RVLBA)
Project name: -Ziway Shalla sub basin water allocation plan (WAP)
Consulting service required for: – Ziway Shalla sub basin water resources potential & demand study
Financing: – Government, Wetland international and IDH-The sustainable Trade Initiative
Expressions of interest
1. This is to announce that Rift Valley Lakes Basin Authority (RVLBA) invites qualified and legal consulting firms to Express their interests to study water resources potential & demand of Ziway Shalla sub basin organized by the Authority in collaboration with Nongovernmental Organizations called IDH-The Sustainable Trade Initiative and Wetlands International. The consulting firms are expected to be qualified, competent, licensed and experienced on water related studies at national and international level and requested to express their interest by submitting their profile to the Authority within fourteen (14) calendar days from the day this announcement is posted on the Herald newspaper.
2. Expression of interest shall be submitted to Rift Valley Lakes Basin Authority Head office, Hawassa, near Tabor primary school.
3. The interested firm should have a consulting license valid for the current and following years (2010& 2011Eth.C), Tin Number, Tax Payer Registration Certificate, Work Permit and registration certificate for VAT.
4. The Authority will identify short listed consulting firms based on their profile after final date of submission of interest expression.
5. After short listed consulting firms are identified, the Authority will invite them for bid.
6. Invited Short listed bidders will obtain bid documents (TOR) from the Authority and submit their financial and technical proposal to the Authority.
Overall objective of the study is to determine current and projected water resources potential and demand of Ziway-Shalla sub basin and subsequent water balance of the sub basin. This shall serve as input for Water Allocation Plan Preparation by the Authority to ensure regulated, efficient and sustainable water use in the sub basin.
The study is needed to be conducted with the consideration that the study area will cover the Ziway–Shalla Sub Basin which is about 14,477 km2 and includes the Lakes and any surface as well as groundwater resources in the sub basin. The consulting body should conduct water resources potential and demand study by taking four watersheds in the sub-basin into consideration. The watersheds are Ketar sub watershed, Meki-sub watershed, and Langano and Shalla watersheds. The study will involve assessment of existing and projected water potential/availability and demand. The water availability projection will be made for thirty years (in three periods 5, 15 and 30 years) and future water demand projection will be forecasted for 5, 15 and 30 years based on government plan that include Oromia National and Southern, Nations, Nationalities &Peoples’ regional states.. The collected water potential and demand data should be analyzed by using appropriate tools to provide the water balance of the sub basin. Key tasks and services expected from the consultant are (the exhaustive list of tasks and services will be available to shortlisted applicants):-
• determining factors of water potential /availability, identify and map surface water resource, assess flows of the Rivers in spatial and temporal pattern, conduct bathometric survey of the Lake Ziway and Abijata, analyze temporal and spatial variation of Rainfall in relation to its impact on water resources, conduct groundwater potential study, estimation of total surface and ground water, determine general status of water resources quality in the sub basin.
• To identify water uses, current and projected demand, conduct water use efficiency, identify water demand determining factors, recommend improved water management options.
• Calculating sub basin water balance based on water availability and demand in the sub basin
• Inception, draft and final reports are required step by step and the total duration allocated for service will be about 8 months.
• The Authority now invites competent consulting firms to indicate their interest in providing the above services. Interested Consultants must provide information indicating their professional capability and experience to perform the services; such information should include (brochures, description of similar assignments, national or international experiences with good performance, willingness and ability to link with international consultancies, interest and commitment to work with Rift Valley Lakes Basin Authority for in house capacity building, clear methodology of the studies, availability of appropriate skills among staff, etc.). Consultants may associate to enhance their qualifications.
• A consultant will be selected in accordance with procedures set out in the bid evaluation criterion of government procurement Agency.
Interested Consultants may obtain further information at the following address during office hour from 8:30 to 5:30P.M local time Monday to Friday.
Expression of interest must be delivered to the address below:
FDRE Rift Valley Lakes Basin Authority
P.O.Box 2162, Hawassa
 Tel +251-462-12-26-67/+251-462-12-30-08
 Fax +251-462-12-30-21
Web: www.rvlba.gov.et
Email: info@rvlba.gov.et

የውሃ አካላት ዳርቻን ለመከለል ለመጠበቅ እና አጠቃቀሙን ለመወሰን በስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ተፋሰስ ባለስልጣን ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለውይይት ቀረበ።

ከዘጠኙ  ክልሎችና  ከሁለቱ  የከተማ  መስተዳደር  ለመጡ  ከፍተኛ  የስራ  ሀላፊዎቸ፣ዩኒቨርስቲዎች  እንዲሁም  ጥሪ  ለተደረገላቸው  ባለድርሻ  አካለት  ረቀቂ  ደንቡ  የቀረበ  ሲሆን የዕለቱንም  የውይይት  መድረክ  የመክፈቻ  ንግግር  በማድረግ  የከፍቱት  የውሃ፣መስኖና ኤኬክትሪክ  ሚኒስቴር  ሚኒስትር  ዶ/ር  ኢንጂነር  ስለሺ  በቀለ  ናቸው፡፡  በንግግራቸውም  ይህ ረቂቅ ደንብ  መዘጋጀት ያስፈለገው በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ  የውሃ አካላት    እየደረሰባቸው  ያለውን ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎችን በመከላከል እና የውሃ አካላቱን ከጥፋት በመታደግ   የዉሃጥራትን  መጨመር፣  የሐይቆች፣  ግድቦችን  ዉሃ  የመያዝ  አቅም  አንዳይዋዥቅ  ማድረግ፣  የአፈርመሸርሸርንም  መቀነስ፣  የአከባቢ  አየር  ነፋሻማነት  መጨመር፣  የዉሃ  አካላት  ዳርቻዎችን  በማልማት በርካታ  የቱሪዝም  አገልግሎቶችንና  የመዝናኛ  ስፍራዎችን  መፍጠር፣ጎርፍ  ሊያስከትላቸዉ  የሚችሉ ጉዳቶችንም  መቀነስ፣በውሃ  ውስጥ  የሚኖሩ  ባዮ  ዳይቨርሲቲ  እንዲጠበቅ  ማድረገግ  ከውሃ የምናገኛቸውን በርካታ ጥቅሞች በዘላቂነት ለመጠቀም  እንድንችል ነው ብለዋል፡፡ በዕለቱም ለረቅቅ ደንቡ መነሻ የሆነው  የውሃ አካለት ደርቻ ነባራዊ ሁኔታን የሚያሳይ የዳሰሳ ጽሁፍ በባለሙያ የቀረበ ሲሆን ይህም ጽሁፍ  በውሃ አካለት ላይ እየደረሰ ያለው ችግር በስፋት ተዳሶበታል፤ከችግሮቹም መካከል የውሃ አካላት ዳርቻ ከእንሰሳት እና ከሰው ንክኪ ነጻ  ባለመሆኑ  የተለያዩ  አካላት  በውሃ  ዳር  ተጠግቶ  የእርሻ  ስራ  መስራት፣ለግጦሽ ከብቶችን  ማሰማራት  እንዲሁም  ከፍብሪካዎች  የሚለቀቁ  ያልታከመ  ውሃ  ወደ  ውሃ አካለት  መለቀቁ  ተጠቃሽ  ችግሮች   ናቸው፡፡  ስለሆነም  አነዚህን  ችግሮች  በዘላቂነት ለመፍታት ባለሰልጣን መ/ቤቱ ተነሳሽቱን ወስዶ  ይህን ረቂቅ ደንብ አዘጋጅቷል፡፡

በረቂቅ ደንቡም የተካተቱት ይዘቶች፡-

         በክፍል አንድ የተካለለቱ ተግባራት የቀረበው

 1. የቃላት ትርጉሜ እና ዓላማ

         በክፍል ሁለት የተካተቱ ተግባራት

 1. የውሃ አካለት ዳርቻን ስለመከለል፣ስለመሰየም እና ስለመመዝገብ
  • የውሃ አካላት ዳርቻዎችን ስለመከለል
  • የውሃ አካላት ዳርቻዎች ጥብቅ ክልል
  • ማንኛውም የውሃ  አካላት  ዳርቸ  ሲከለል  እና  ሲሰየም  መደረግ  ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች
 2. በተከለሉ የውሃ አካላት ዳርቻዎች ዙርያ የተከለሉ ድርጊቶች ምን ምን እንደሆኑ
 3. የተከለሉ የውሃ አካላት ዳርቻዎች ጥበቃ እና አስተዳደር
 4. ጥፋት ሲጠፋ የመጠቆም ግዴታ

ክፍል ሶስት

 1. ስለተከለሉ የውሃ አካላት ዳርቻ ተቆጣጣሪዎች ስልጣንና ተግባር
 2. የክልሎች ስልጣንና ተግባር
 3. ይግባኝ ስለመጠየቅ መብት
 4. ስለመክሰስ መብት

ክፍል አራት

 1. ጥፋትና ቅጣት
 2. ከተቆጣጣሪዎቸ ጋር በተያያዘ ስለሚፈጸሙ ጥፋቶች
 3. የውሃ አካላት ዳርቻን ለጎዱት ሚያጋልጡ ድርጊቶች ጋር በተያያዘ ስለሚፈጸም ወንጀል
 4. ስለመውረስ እና ወደ ነበረበት ሁኔታ ስለመመለስ

ክፍል አምስት

 1. ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
 2. መመሪያ የማውጣት ስልጣን
 3. ተፈጻሚነት የሌላቸው ደንቦች
 4. የደንቡ መፈጸሚያ ጊዜ

ባአጠቃላይ  ለግብዓት  የቀረበው  ረቂቅ  ደንብ  እነዚህን  ጉዳዮች  የያዘ  ሲሆን ከተሳታፊዎችም  በርካታ  ግብዓት  የሚሆኑ  ሀሳቦች  ቀርበዋል፡፡  የቀረቡትንም ሀሳቦች  በመውሰድ  ለቀጣይ  ደንቡን  አዳብሮ  ለሚመለከተው  አካል  ለማቅረበረ ዝግጅት ተጀምሯል፡፡

የአባያ ጫሞ ሀይቆች በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች መዳረጋቸው ተገለጸ

ከ180 ሄክታር በላይ በሆነ የሀይቆቹ ዳርቻ መሬት ላይም የእምቦጭ አረም መከሰቱ ታውቋል

የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ተፋሰስ ባለሥልጣን በአባያ ጫሞ #ሰገንና ወይጦ ንዑስ ተፋሰስ በውጤታማ የውሃ ሀብት አያያዝና አጠቃቀም ዙሪያ ከተለያዩ ባለድርሻ  አካላት ጋር የመከረ ሲሆን\ በመድረኩም ላይ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኢነተር ዩኒቨርስቲ ኮርፖሬት ፕሮግራም ማናጄር ዶ/ር ፋሲል እሸቱ በተፋሰሱ ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት መጠን መንስኤና መፍትሄ አስመልክተው ጥናት አቅርበዋል።

የእንቦጭ አረምን ጨምሮ በተለያዩ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች የውሃ መጠናቸውንና ጥራታቸው ለአደጋ ከተደረጉት የተፋሰሱ አከባቢዎች መካከል ደግሞ በቱሪስት መስህብነታቸው የሚታወቁት የአባያና የጫሞ ሀይቆች መሆናቸወን ጥናቶቹ አሳይተዋል።

በላይኛው ተፋሰስ አከባቢዎች የተጠናከረ የአፈርና የውሃ ጥበቃ  ስራ ባለመሰራታቸው የተነሳ  በጎርፍ ደለል መሞላታቸው  የሀይቆቹ \ዳርቻዎች በእርሻ ስራ #ግጦሽ #ደን ጭፍጨፋና በመሳሰሉት ተግባራት ከሰውና እንስሳት ንክኪ ነፃ ያለመሆናቸው  ለሃይቆቹ መጠን መቀነስ ምክንያቶች ከሆኑት መካከል ዋነኞቹ እንደሆኑም በጥናቶቹ ተመልክቷል።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ ከ800 ሜትር በላይ ርዝመት ያለው የሀይቆቹ አካል ውሃው ነጥፎ ወደ ደረቅ መሬትነት እንደተለወጠ ጥናቱ ያሳያቸው የአባያና ጫሞ ሀይቆች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከ187 ሄክታር በላይ የቆዳ ስፋት ያለው የእንቦጭ አረም በሀይቆቹ ዳርቻዎች በፍጥነት እየተዛመተ መገኘቱ ለሀይቆቹ መድረቅ ሌላውና ትልቁ ስጋት ሊሆን እንደሚችልም በጋሞ ጎፋ ዞን አከባቢና ደን ጥበቃ ጽ/ቤት  የብዝሃ ህይወት ልማት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ ጋመቡራ ገንታ ባቀረቡት ጽሁፍ አሳይተዋል።

የአከባቢውን ህዝብ በዋነኛነት በማሳተፍ አረሙን ለማስወገድና ለመከላከል ስራዎች የተጀመሩ ቢሆንም አዞና ጉማሬን ጨምሮ ሃይቆቹ ከሏቸው አደገኛ እንስሳት አንፃር በሰው ጉልበት ብቻ የማይደፈር በመሆኑ መንግስትና ባለድርሻ አካላት አፋጠኝ ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባም መድረኩ ትኩረት ሰጥቶታል።

የስምጥ ሸለቆ ሃይቆች ተፋሰስ ባለስልጣን በተፋሰሶቹ አከባቢ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል መጠነ ሰፊ ሥራዎች ሲያከናውን የቆየ ቢሆንም በሚፈለገው ፍጥነት አደጋዎቹ ሲቀነሱ ባለመቻላቸው ትልቅ ስጋት ውስጥ መሆናቸው የገለፁት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ከበደ ካንቹላ ባለድርሻ አካላት ህዝቡን አቀናጅቶ በማነቃነቁ ረገድ ትኩረት ሰጥተው ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የተከሰተውን አሳሳቢ ችግር በዘላቂነት ለማስወገድ ባለስልጣኑ በቴክኒክ እና በፋይናንስ ለባለድርሻ አካላት ሲያደርግ የቆየውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ በሀይቆች ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው ጉዳት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አመራሩና ህዝቡ ተገንዝቦ ተፋሰሶችን ከአደጋዎች ሊታደግ ይገባል ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።